Podcast Cover

Amharic

  • በተራራው ስብከቱ ላይ ያለው አውድ

    30 DEC 2022 · የተራራው ስብከት ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በእርሱ መልዕክትና በእርሱ ብርታት ወደ ዓለም እንዲሄዱ የሰጠው መሰረታዊ አስተምህሮና ስልጠና ነው፡፡ በዚህ ክፍል በጣም ታዋቂ የሆነው ነገር ግን ሰዎች ያልተረዱትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልን እንማራለን፡፡ ከኢየሱስ የፈውስ አገልግሎት የተነሳ በርካታ ሰዎች ተከትለውት ነበር፣ ኢየሱስ የእርሱን ተከታዮች ለሰው ልጆች ችግሮች የእርሱ መፍትሄ አካል እንዲሆኑ ወደ ተራራው ስብከት ጋበዛቸው፡፡
    Played 24m 25s
  • ስብከት አንዴ የተራራው ሊይ ስብከት አውዴ

    30 DEC 2022 · በጣም አስፈላጊ በሆነው የተራራው ስብከት ኢየሱስ በገሊላ በሚገኝ ተራራ ላይ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ነን የሚሉትን ሰዎች የሞገተበት፣ ደቀ መዛሙርቱን በእግዚአብሔር ፍቅርና በዓለም ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በሚያሰቃይ ሕመም መካከል ስልታዊ በሆነ መንገድ ያስቀመጠበት ነው፡፡ እርሱ የራሱን ደቀ መዛሙርት ከእርሱ ጋር አብረው እንዲሰሩና የእርሱ ፍቅር አስተላላፊዎች እንዲሆኑ ሞገታቸው፡፡ እርሱ የተራራውን ስብከት ያጠናቀቀው አድማጮቹ ለእርሱ የተሰጡ እንዲሆኑና 12ቱን ሰዎች ሐዋርያት፣ ወይም “የተላኩ” ብሎ በመመደብ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ለኢየሱስ ኖረው ለኢየሱስ የሞቱ ናቸው፡፡
    Played 25m 24s
  • ስብከት ሶስት እኔ አሌችሌም እርሱ ግን ይችሊሌ

    30 DEC 2022 · ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ማስተማር የጀመረው በስምንት ባሕርያት ሲሆን እነርሱም “ብፁዓን” ተብለው የሚታወቁት ናቸው፡፡ ኢየሱስ እነዚህ ባሕርያት ላሉአቸው ደቀ መዛሙርት ሊባርካቸው ቃል ገባ፡፡ እነዚህ የተባረኩ ባሕሪያት የአመለካከት ግለ - ታሪክ ወይም አስተሳሰብ ሲሆኑ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርትን ባሕሪይ ላይ ተፅዕኖ የሚያመጡና የእርሱ መፍትሄ አካልና በምድር ላይ ለሚሰቃዩ ሰዎች የክርስቶስ መልስ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ የእነዚህ ባሕሪያት የመጀመሪያው “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡” የሚለው ነው፡፡
    Played 23m 59s
  • ስብከት አራት የማፅናናት አገሌግልት እና እረፍት

    30 DEC 2022 · ደቀ መዛሙርቱ ማዘንና የዋህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ መማር አለባቸው፡፡ አማኞች አንዳንድ ጊዜ የሃዘን ምልክትን ማሳየት ስህተት ነው ብለው ያስባሉ፡፡ የእኛን ሃዘን ትክክለኛውን ጥያቄ እንድንጠይቅ፣ መልስን ከእግዚአብሔር እንድንፈልግ፣ እና እግዚአብሔር ያዘጋጀውን በረከት እንድንቀበል ለመጠቀም እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ በምድር ላይ ከኖሩ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ሙሴ ትሁት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል፡፡ የዋህነት ማለት በአዛዥ ቁጥጥር ሥር መሆን ነው፡፡ የዋህ ደቀ መዝሙር በእግዚአብሔር አብ ቀንበር ሥር በስነሥርዓት የሚኖር ነው፡፡
    Played 30m 18s
  • ስብከት አምስት የተሇየ ፅዴቅ

    30 DEC 2022 · ለጽድቅ መራብና መጠማት ትክክለኛን ነገር ለማወቅ በጥልቅ ፍላጎት መፈለግ ነው፡፡ እንዴት እንደምታደርጉና ምን እንደምታደርጉት ለእግዚአብሔር አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ እኛ የተጠራነው ትክክለኛውን ነገር እንድናደርግ ነው እንጂ ምቹ ነገሮችን እንድናደርግ አይደለም፡፡ ብፁዓን በሚለው ትምህርት ውስጥ ንድፍን እንመለከታለን፡፡ እነዚህ ብፁዓን በሚለው ትምህርቶች ውስጥ ሁሉም የቀረቡት ጥንድ ጥንድ ሆነው፡፡ እኛ የምናዝነው በመንፈስ ድሆች እየሆንን ነው፣ እኛ የዋሆች ስንሆን ለጽድቅ እንራባለን እንጠማለን፡፡ የተሰጠን ተስፋ ሙሉ በሙሉ እንደምንሞላ ነው፡፡
    Played 23m 41s
  • ስብከት ስዴስት የፍቅር ሌብ

    30 DEC 2022 · “የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፣ ይማራሉና፡፡ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፣ እግዚአብሔርን ያዩታልና፡፡” “ምሕረት” ሚለው ቃል “ቅድመ ሁኔታ የሌለበት ፍቅር” ማለት ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ፍቅር ደቀ መዛሙርቱ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለሌሎች ማስተላለፍ የሚችሉ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ነው፡፡ እኛ የምሕረት ሰዎች ስንሆን የእኛ ፍላጎት ጥያቄ ላይ ይወድቃል ምክንያቱም ቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ፍቅርን ለመረዳት ከባድ ስለሆነ ነው፣ በተለይም የዚህን ዓይነት ፍቅር አይተው ለማያውቁ ሰዎች፡፡ እግዚአብሔር እኛን በወደደበት ፍቅር እኛም ሌሎችን ስንወድድ ፍላጎታችን ንፁህ ይሆናል፡፡
    Played 22m 45s
  • ስብከት ሰባት የእርቅ አገሌግልት

    30 DEC 2022 · ሰባተኛው ብፁዓን (የሚያስታርቁ ብፁዓን ናቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና) የሚናገረው የእግዚአብሔር መፍትሄ ተልዕኮ አካል ለሆኑት ነው፡፡ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ተለይተዋል፡፡ እና ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን - ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት ትክክለኛ ከሆነ - ሌሎችን ከእርሱ ጋር እንድናስታርቅ እግዚአብሔር ይጠቀምብናል፡፡ እንዲሁም እርሱ እኛ እንድንታረቅና ሌሎችም እንዲታረቁ ይረዳቸዋል፡፡
    Played 21m 20s
  • ስብከት ስምንት የተሰዯደ የሰሊም መሌክተኞች እና ተስፋዎች

    30 DEC 2022 · “ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡” የሚያስታርቁ ብፁዓን የሚለውን ተከትሎ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው የሚለው መጠቀሱ ምክንያት አለው፡፡ እነዚያ የእርቅ አገልግሎት አገልጋዮች ብዙ ጊዜ መከራን ይቀበላሉ፣ ሕይወታቸውንም የሚያጡበት ጊዜ አለ፣ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸውን የኢየሱስ ወገን ስላደረጉ ነው፡፡ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት፣ በኢየሱስ የሚኖሩ፣ “የብፁዓን” ባሕርይ ያላቸው፣ ሰዎች መሆን እንዳለባቸው እንዲሆኑ በመልካም ሥነ ምግባር ሰዎችን የሚሞግቱ ብዙ ጊዜ ለኢየሱስ መከራን ይቀበላሉ፡፡
    Played 17m 31s
  • ስብከት ዘጠኝ ባህሌ እና ባህሪይ

    30 DEC 2022 · ብፁዓን የኢየሱስ የተራራው ስብከት መሠረታዊ ሐሳቦች ናቸው፡፡ እነዚህ ብፁዓን ዓለምን የሚለውጡትን መልካም ባሕርያት የሚገልፁ ናቸው፡፡ ቀጥሎ ኢየሱስ የእርሱ ደቀ መዛሙርት የሚኖሩበትን ባህልና ሕብረተሰብ እንዲለውጡ ማብራሪያና የትግበራን ትምህርት ሰጥቷል፡፡ ደቀ መዛሙርት ክርስቶስን በሚመስል ባሕርይ የዓለምን ሕዝብ ሲያገለግሉ፣ እነርሱ ሥጋን ከመበስበስ እንደሚጠብቅ ጨው፣ የእነርሱ ተፅዕኖ ዓለምን ከመጥፋት ያድናል፣ እነርሱም ጠቃሚ የሆኑ ኢየሱስ የሚጠቀምባቸው አስፈላጊ ሰዎች ይሆናሉ፡፡
    Played 22m 23s
  • ስብከት አስር ጨው እና ብርሃን

    30 DEC 2022 · እውነተኛ ደቀ መዛሙርት መደበቅ የማይችሉት እውነት ኢየሱስ እነርሱን የባህል ለውጥ እንዲያመጡ እንደሚጠቀምባቸው ነው፡፡ የእርሱ ደቀ መዛሙርት በተራራ ላይ እንዳለች ከተማና በመቅረዝ ላይ እንዳለ ሻማ ናቸው፡፡ በጨለማ ለሚገኙ እጅግ በርካታ ሰዎች ብቸኛ ብርሃን ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው፡፡ የእርሱ ደቀ መዛሙርት ጨው እና ብርሃን የመሆን ሚናቸውን ካልተወጡ ማንም ሊወጣው አይችልም፡፡ደቀ መዛሙርት ወደ አለም የተላኩት የእግዚአብሔርን መፍትሄ ሁሉም ሰው እንዲያንጸባርቁ ነው፡፡
    Played 21m 11s
Information
Author Foundations by ICM
Categories Christianity
Website -
Email -

Looks like you don't have any active episode

Browse Spreaker Catalogue to discover great new content

Current

Podcast Cover

Looks like you don't have any episodes in your queue

Browse Spreaker Catalogue to discover great new content

Next Up

Episode Cover Episode Cover

It's so quiet here...

Time to discover new episodes!

Discover
Your Library
Search